የ እኔነቴ፣የህይወቴ ቋሚ መሠረት
ሢሣዬ
ምንዳዬ
ዋርካዬ
ዋልታ መከታዬ ፍጹም ለእኔነቴ
የደጃፌ አጥር
የቤቴ ማገር
ሞገሥና ክብር
ጥላ ከለላዬ ዋሱ ጠበቃዬ
፧ጥልዬም፧እንዲህ አለ
መለያየት ሞት ነው፣ለተዋደደ ሠዉ
ስቃዬን አሳየኝ ደርሶብኝ ብቀምሠው
ሳትሠናበተኝ ሳልሠናበትህ
የመኖሩ ህልምህ፤ጽኑ ፍላጐትህ
ተጨናፈገና በሞት ፅልመት ነጐድህ
ወደዘላለማዊው ቤትህ፤ዮናስን ጥለህ ጨክነህ መሄድህ
መሪር ነው፣ጥልቅ ነው ሀዘኔ
ላትጐድል ከአይኔ
ሳጣህ ከአጠገቤ
ሰትርቀኝ ከእኔ
አስፍዬ ብርሀኔ
አፈሩን ገለባ፤ነፍስህን በገነት
ጌታ ያኑርልኝ በዘላለማዊው ህይወት
ከባለቤቱ፦ወይዘሮ ሠብለ እሸቴ