January 15, 2023
January 15, 2023
በዛሬው ቀን የታዴን ሁለተኛ የሙት አመት በማክበር ወንድማችንን እንድናስታው ተሰብሰበናል ፣ አወን ሁለት አመት ሆነ ታዴ ከተለየን ፣ የዛሬ ስድስት ወር ገደማ ፣ አዲስ ፍሬ ት/ትቤ በታዴ ስም የጽሃፍት ቤቱን ሲያመርቅ ያነበብኩትን አጭር ጽሁፍ ከዘመድ ወዳጆቹ ጋር በመቋደስ የታዴን በጎ ስራዎች ማስታወስ ደስታዬ ነው ፣
ዘሪሁን ተክሌ .፣ ጥር 7 ፣ 2015
በአዲስ ፍሬ አንደኛ ደረጃ ት/ቤት ታደሰ ገሰሰ መጽህፍት ቤት ምረቃ/ 8 ጁን 2022.
ወንድማችን ታደሰ ከተለየን ሰነበተ ፣ አመት ፣ አመት ተኩል አለፈው....አሁንም ለዘላለም እንደተለየን ልቀበለው አልቻልኩም ፣ አልፈለኩም ፣ አሁንም ቀበሌ 19 ፣ የቼዝ ገበታው ፊት፣ በአርምሞ ሲያስብ ይታየኛል ፣፣
ከታደሰ ምንም ጊዜ የማልረሳው እንድ ትልቅ ቁም ነገር አለ ፣ ከሚወዳቸው ጥቅሶች አንዱ “ ደግነት ለራስ ነው ” የሚለው ነው ፣ ከዚህ ጥቅስ ጋር አንድ የተለየ ታሪክ አለኝ ፣ ታደሰ በብዛት እና በአይነት የላቁ የፊልም ፣ የሙዚቃ፣ የመጽሃፍት ፣ የልዩ ልዩ መጣጥፎች እራሱ የጻፋቸው እና ከሌሎችም ደራስያን የሰበሰባቸው ሰፊ ኮሌክሽን እንዳለው ብዙ ሰው ያውቃል፣፣ በየጊዜው የተወሰኑ የፊልም አይነቶች፣ አንዳንድ ዘፈኖች ፣ ከጻፋቸው ጽሁፎች የወቅቱን ሁኒታ ያብራራሉ ብሎ የሚገምታችውን በሲዲ ፣ በሜሞሪ ስቲክ እየቀረጸ ይሰጠኛል ፣ እንድ ቀን እንደውም በሙሉ የሃርድ ዲስኬን እንዳለ ለምን አልገለብጥልህም፣ ከፍ ያለ የክምችት ካፓሲሲቲ ያለው ኤክስተርናል ዲስክ ይዘህ መጥተህ በሙሉ ያሉኝን ፋይሎች ልገልብጥልህ አለኝ ፣ እኔም በደስታ ተቀበልኩት ፣ ይሰነብትና የታደሰ ኮምፑተር ይሰረቃል ፣ ታደሰም ይደውልና “ደግነት ለራስ ነው ብዬህ የለ ፣ ኮምፑተሬ ተሰርቆ ሌላ ኮምፑተር ገዝቼአለሁ ፣ በል ፋይሎቼን መልስ “ አለኝ ፣፣ ከዚህ ያገኘሁት ትምህርት ፣ ደግነት ለአድራጊው ከሚሰጠው ደስታ እና ጸጋ ጋር አድራጎቱ ይዋል ይደር አንጂ ተመልሶ ለደግ አድራጊው ፣ ለባለቤቱ የሚመጣ መሆኑን ነው ፥፣ አሁንም አንድ ሰው ከመንገዱ ወጥቶ ለሌላው ሰው በጎ ነገር ሲሰራ ሳይ ፣ የታዴ ምስል ከፊቴ ድቅን ይላል ፣፣
ከሮታሪ ክለብ አዲስ አበባ እንጦጦ ወንድሞቹ እና እህቶቹ ጋር የአዲስ ፍሬ ት/ትቤን ለተማሪዎቹ ፣ ለመህራን፣ እንዲሁም ባጠቃላይ ለት/ቤቱ ማህረሰብ ምቹ ለማድረግ ታዴ ያላደረገው ጥረት የለም ፣ ለዚህም የአዲስ ፍሬ ማህበረሰብ ለታዴ ያለው አክብሮት እና ፍቅር ህያው ምስክር ነው፣፣ በተለይ ለትምህርት ጥራት ፣ ለእውቀት መዳበር የነበረው ጥጽኑ እምነት እና ጥረት የላቀ ነበር ፣ የት/ቤቱ መጻህፍት ቤት በወንድማችን በታደሰ ስም መሰየሙ ትክክል እና ተገቢ ነው ፣ ይህን በማድረግ መልካም ፈቃደኝነታቸውን እና ድጋፋቸውን ለሰጡን ለት/ቤቱ አመራር እና መምህራን ምስጋናችን ከፍ ያለ ነው፣ ይህ መጽሃፍት ቤት በት/ቤቱ ውስጥ ተገቢ ቦታውን ይዞ ‘’የእውቀት ማእከል’’ እንዲሆን የተቻለውን ጥረት ለማድረግ በሮታሪ ክለብ አዲስ አበባ እንጦጦ ስም ቃል እገባለሁ ፣፣
የታደሰን ነብስ በገነት ያኑርልን ፣፣
ዘሪሁን ተክሌ ፣ ሮታሪ ክለብ አዲስ አበባ እንጦጦ፣ የ2021/2022 ሊቀ መንበር