ForeverMissed
Large image
Stories

Share a special moment from W/ro. Botaneshe's life.

Write a story

«ሦስት ነገሮችን ተምሬያለሁ»

June 21, 2015

የአንድ ኩባንያ ባለቤት ለደርጅቱ ብቁ የሆነ ሥራ አስኪያጅ ለመቅጠር ማስታወቂያ አወጣ፡፡ ላወጣው ማስታወቂያ ባቀረቡት ማስረጃ ተወዳድረው ካለፉት ሦስት ሰዎች መካከል በዕድሜ ትንሽ የሆነውን ለቃለ መጠይቅ ጠራው፡፡

ወጣቱ በተጠራበት ቀን አለባበሱን አሳምሮ መንፈሱንም አንቅቶ ጠበቀ፡፡ የኩባንያው ባለቤት የወጣቱን የትምህርት እና የሥራ ሁኔታ የሚገልጠውን መረጃ አገላብጦ አየው፡፡ የተማረው በሀገሪቱ ውስጥ አንቱ በሚባሉ ት/ቤቶች ነው፡፡ የመጀመርያ እና ሁለተኛ ዲግሪውን የሠራው እጅግ በጣም ሀብታሞች በሚማሩባቸው ኮሌጆች ውስጥ ነው፡፡ ያገኛቸው ውጤቶች ምርጥ ከሚባሉት ውጤቶች ውስጥ ናቸው፡፡ በየደረጃው ከነበሩ መምህራን እና የትምህርት ባለሞያዎች ሽልማቶችን እና ማበረታቻዎችን አግኝቷል፡፡
የኩባንያው ባለቤት «ይህንን ሁሉ የትምህርት ክፍያ ይከፍልልህ የነበረው አባትህ ነው» ሲል ጠየቀው፡፡ ልጁም «አይደለም፤ አባቴን በልጅነቴ ነው ያጣሁት» ሲል መለሰለት፡፡ «ኦ ይቅርታ፤ ታድያ ስኮላርሺፕ አግኝተህ ነበር» አለው፡፡

«እስካሁን በትምህርት ጉዞዬ ስኮላርሺፕ የሚባል አላጋጠመኝም» ብሎ ፈገግ አለ፡፡

«መቼም ከዘመዶችህ አንዱ የተሻለ ገቢ ያለው ሰው መሆን አለበት» አለና የኩባንያው ባለቤትም ፈገግታውን በፈገግታ መለሰለት፡፡

«እኔ ሀብታም ዘመድ የለኝም፤ ኧረ እንዲያውም ዘመድ ራሱ የለኝም» አለው ወጣቱ፡፡

የኩባንያው ባለቤት እየተገረመ «ታድያ ይህንን በመሰሉ ት/ቤቶች ገብቶ ለመማር እኮ ከፍተኛ ገንዘብ ይጠይቃል፤ ማን እየከፈለልህ ነበር የምትማረው» ሲል በአግራሞት ጠየቀው፡፡

«የምትከፍልልኝ እናቴ ነበረች» አለና ወጣቱ በኩራት መለሰ፡፡

«እናትህ ምን ዓይነት ሥራ ነው የምትሠራው» አለው ባለቤቱ፡፡

«እናቴ የሰዎችን ልብስ እየሰበሰበች የምታጥብ ሴት ናት» አለው ወጣቱ፡፡

«ልብስ እያጠበች ነው አንተን ይህንን በመሳሰሉ ት/ቤቶች ያስተማረችህ)»
«አዎ»

«አንድ ጊዜ እጅህን ለማዬት እችላለሁ» አለው የኩባንያው ባለቤት፡፡ ወጣቱ እጁን ወደ ባለቤቱ ላከው፡፡ እጁ ከኬክ የለሰለሰ ነበረ፡፡

«ለመሆኑ እናትህን በልብስ አጠባው ረድተሃት ታውቃለህ»

«አላውቅም»

«ለምን)»

«እናቴ እኔ ምንም ሥራ እንድሠራ አትፈልግም፤ እንድማር፣ እንዳጠና እና እንዳልፍ ብቻ ነው የምትፈልገው፤ ስለዚህ ሥራ ሠርቼ አላውቅም»

«በጣም ጥሩ» አለ የኩባንያው ባለቤት «ቃለ መጠይቁን ነገ እንቀጥላለን፤ አሁን ወደ ቤትህ ሂድና አንድ ነገር አድርግ» አለው፡፡

ወጣቱ እየገረመው «ምን» አለ፡፡

«የእናትህን እጆች እጠብ፤ ከዚያ የሆነውን ነገ ትነግረኛለህ»

በቃለ መጠይቁ የተሻለ ነገር አድርጌያለሁ ብሎ እያሰበ በደስታ ወደ ቤቱ ሄደ፡፡

ቤቱ ገብቶ እናቱን እጇን ለማጠብ ጠየቃት፡፡ አዲስ ነገር ሆነባትና ጠየቀችው፡፡ እርሱም ዛሬ ያጋጠመውን ነገር አጫወታት፡፡

ውኃ እና ሳሙና አቀረበና የእናቱን እጆች ማጠብ ጀመረ፡፡ የተኮራመቱ፤ የተሰነጣጠቁ፤ የቆሳሰሉ፤ የተጠባበሱ፤ እጆች፡፡ የእርሱን እና የእናቱን እጆች እያስተያየ ማልቀስ ጀመረ፡፡ ከሚያጥብበት ውኃ ይልቅ እርሱ የሚያነባው ዕንባ በለጠ፡፡ እነዚህ እጆች እንዲህ የሆኑት እርሱን ለማስተማር መሆኑን አሰበ፡፡ እነዚህ ጠባሶች የእርሱ ጠባሶች ናቸው፡፡ እነዚህ ቁስሎች የእርሱ ቁስሎች ናቸው፤ እነዚህ እጆች ናቸው ለእርሱ የትምህርት ውጤት መሠረቶቹ፣ እነዚህ እጆች ናቸው እርሱን ለአካዳሚያዊ ውጤት ያበቁት፤ እነዚህ እጆች ናቸው ዛሬ ለቆመበት ታላቅ ደረጃ ያበቁት፡፡

የእናቱን እጆች አጥቦ ሲጨረስ የቀሩትን ልብሶች ሁሉ ከእናቱ ጋር አጠበ፡፡ በዚያች ሌሊት ያ ልጅ ከእናቱ ጋር ለረዥም ሰዓት ሲያወሩ አደሩ፡፡ ነግራው የማታውቀውን ታሪክ ነገረችው፤ ሰምቶት የማያውቀውን ታሪክም ሰማ፡፡

በማግስቱ ወጣቱ ወደ ኩባንያው ባለቤት ዘንድ ሄደ፡፡ የኩባንያው ባለቤት የወጣቱን ዓይኖች ሲያይ የዕንባዎቹን ፈለግ ተመለከተ፡፡ እናም «ትናንት ያደረግከውን እና ያጋጠመህን ልትነግረን ትችላለህ)» ሲል ጠየቀው፡፡
«የእናቴን እጆች አጠብኳቸው፡፡ የእናቴ እጆች እንደዚህ መሆናቸውን አላውቅም ነበር፡፡ ብዙ ነገር ነገረችኝ፤ ልብሶቹንም አብሬያት አጠብኩ» አለው፡፡

«ታድያ ምን ተማርክ» አለው የኩባንያው ባለቤት፡፡

«ሦስት ነገሮችን ተምሬያለሁ» አለ ወጣቱ፡፡ «መጀመርያ ነገር አድናቆት እና ምስጋናን ተምሬያለሁ፡፡ እናቴ ባትኖር ለእኔም ያንን ሁሉ መከራ ባትቀበል ኖሮ ዛሬ የደረስኩበት ልደርስ አልችልም ነበር፡፡ ስለዚህ እናቴን ምንጊዜም ላመሰግን፤ በሄድኩበት ቦታ ሁሉ ቀድሜ ስሟን ልጠራ፤ ስለ ራሴ ከመናገሬ በፊት ስለ እርሷ ልናገር እንደሚገባ ተረድቻለሁ፡፡ ሁለተኛ ደግሞ እናቴ ያለፈችበትን እውነተኛው ነገር መረዳት የቻልኩት አብሬያት ሆኜ ሥራዋን ስጋራት ነው፡፡ በሱታፌ ካልሆነ በቀር በነቢብ እና በትምህርት ብቻ የአንድን ነገር ርግጠኛ ጠባይ እና ሁኔታ መረዳት አይቻልም፡፡ ሦስተኛ ደግሞ በአንድ ቤተሰብ ውስጥ መኖር ብቻ ሳይሆን ቤተሰባዊ ትሥሥርም ወሳኝ መሆኑን አይቻለሁ፡፡» አለው

የኩባንያውም ባለቤት «የምፈልገው ሥራ አስኪያጅ አሁን ተገኘ፡፡ ለእርሱ ሕይወት ሌሎች የከፈሉትን ሰማዕትነት የሚረዳ፤ አብሮ በመሥራት ችግሮችን መቅመስን እና መፍታትን የተማረ፤ የሥራ ግቡ ገንዘብ ማግኘት ብቻ ያልሆነ ሰው አሁን ተገኘ» አለና ቀጠረው ይባላል፡፡

ከኛ ሕይወት ጀርባ ስንት ሰዎች አሉ) ለመሆኑ ዋጋ እንሰጣቸዋለን) እናመሰግናቸዋለን) ስማቸውን እንጠራለን) የቀመሱትን መከራ እናውቅላቸዋለን) ችግራቸውን እንሳተፍላቸዋለን)
ፕሬዚዳንት፣ ጠቅላይ ሚኒስትር፣ ሚኒስትር፣ ፓትርያርክ፣ ጳጳስ፣ ሼህ፣ ዑላማ፣ ምሁር፣ ሳይንቲስት፣ ነጋዴ፣ አትሌት፣ አርቲስት፣ ሰባኪ፣ ፓስተር፣ ሐኪም፣ ፖለቲከኛ፣ ገበሬ፣ ጋዜጠኛ፣ ደራሲ፣ ወዘተ፣ ወዘተ ስንሆን ብቻችንን ነበርን እኛ እዚህ እንድንደርስ ስንቶች ሰማዕትነት ከፈሉ) የስንት ሰዎች ወዝ ፈሰሰ፣ ላብ ተንቆረቆረ፣ ገንዘብ ተከሰከሰ፣ ጨጓራ ተላጠ፣ አንጀት ተቃጠለ)
አምፖሎቹ ዝም ብለው አልበሩም፡፡ አምፖሎቹ እንዲበሩ ያደረገው ጀነሬተሩ ነው፡፡ ጀነሬተሩ ግን አይታይም፡፡ የሚታዩት አምፖሎቹ ናቸው፡፡ ሰዎችም የሚያውቋቸው አምፖሎቹን ነው፡፡ አብዛኛው ሰው አምፖሎቹን ለማሳመር እና በአምፖሎቹ ውበትም ቤቱን ለማሳመር ይጥራል እንጂ ስለ ጀነሬተሩ አይጨነቅም፡፡ ወሳኙ ግን እርሱ ነው፡፡
ጀነሬተሮቻችን እነማን ናቸው፡) እነዚህ ጀነሬተሮች ናቸው በሃይማኖት ቅዱሳን፣ በሀገር ቀደምት አባቶች፣ በዕውቀት ፋና ወጊዎች፣ በነጻነት አርበኞች፣ እየተባሉ የሚጠሩት፡፡ ያለ እነዚህ እምነት፣ ሀገር፣ ነጻነት፣ ክብር፣ ዕውቀት፣ ጥበብ፣ ሳይንስ፣ ቴክኖሎጂ፣ ዕድገት፣ ብልጽግና የሚባሉ ቃላት ውኃ አይቋጥሩም ነበር፡፡

የዚያ ልጅ ችግሩ መማሩ አልነበረም፣ የተሻለ ውጤት ማምጣቱም አይደለም፤ የተማረበትን እና የተሻለ ውጤት ያመጣበትን ምክንያት መርሳቱ ነው፡፡ መማሩን ያውቃል፤ እንዴት ሊማር እንደቻለ ግን አያውቅም፡፡ ለዚያ ውጤት ያበቃው ማጥናቱ፣ ተግቶ መሥራቱ እና የአእምሮ ብቃቱ ብቻ መስሎ ሊታየውም ይችላል፡፡ ግን አይደለም፡፡ እነዚህ ሁሉ መሠረታቸው እናቱ ናት፡፡ እናቱ መሥዋዕትነትን ለመክፈል ዝግጁ ባትሆን ኖሮ እነዚህ ሁሉ ገደል ይገቡ ነበር፡፡ ስንት አእምሮ ያላቸው ሰዎች ደጋፊ በማጣት ጎዳና ላይ ቀርተዋልኮ፤ ስንት ተግተው ማጥናት የሚችሉ ጎበዝ ተማሪዎች አጋዥ በማጣት አቋርጠዋልኮ፡፡

ለቀደምቶቻችን ዋጋ ካልሰጠን ለኛ ዋጋ የሚሰጥ ትውልድ አይፈጠርም፡፡ መነሻችንን ካላወቅን በመድረሻችን አናመሰግንም፡፡ ችግሮችን ካልቀመስን አማራሪዎች እና ጨካኞች እንሆናለን፡፡ ለእኛ ሕይወት ሌሎች ለከፈሉት ዋጋ ካልሰጠን እኛም ለሌሎች ሕይወት ምንም አንከፍልም፡፡ እኛ እንድናድግ ያደረጉትን ከዘነጋን ሌሎች እንዲያድጉ አናደርግም፤ ለኛ ሲባል ቀደምቶቻችን የቀመሱትን መከራ ካላሰብን እንዴትስ ለሌሎች ብለን መከራ እኛ እንቀምሳለን
ሕይወት እንደ አውሮፓ ዋንጫ ጥሎ ማለፍ አይደለችም፡፡ ይዞ ማለፍ እንጂ፡፡ ምኒሊክን እየናቅን አዲስ አበባ ላይ መኖር፤ ዐፄ ፋሲልን ረስተን ጎንደር ግንብን ማስጎብኘት፤ ንግሥተ ሳባን ዘንግተን አኩስም ጽዮንን ማንገሥ እንዴት ይቻላል ኃይሌ ገብረ ሥላሴን ያለ አበበ ቢቂላ እንዴት ማሰብ ይቻላል
እናቱም ይህንን ሁሉ ብታደርግም አንድ የሚቀራት ነገር ግን ነበር፡፡ አልነገረችውም፡፡ የስኬቱን ምሥጢር አልነገረችውም፡፡

ወላጆች ለልጆቻቸው መንገር አለባቸው፡፡ የሚገዛው ኬክ፣ የሚገመጠው ዳቦ፣ የሚጫወቱበት መጫወቻ፣ የሚዝናኑበት ገንዘብ፣ የሚማሩበት ምርጥ ት/ቤት ክፍያ፣ የሚለብሱት ውድ ልብስ፣ የሚተኙበት ምቹ አልጋ እንዲሁ እንደ እንግዳ ደራሽ እንደ ውኃ ፈሳሽ የመጣ አይደለም፡፡ ደም ተተፍቶበት የተገኘ ነው፡፡ ይህንን ማወቅ አለባቸው፡፡ ቢያንስ ቢያንስ ሌላ ማድረግ ቢያቅታቸው የወላጆቻቸውን ሻካራ እጆች ማጠብ አለባቸው፡፡ ስሜቱን ስሜታቸው፣ ጉዳቱን ጉዳታቸው ማድረግ አለባቸው፡፡ ያለበለዚያ ወላጆ ቻቸውን አያመሰግኑም፣ አያደንቁም፣ አያከብሩም፡፡

የበሉበትን ወጭት መሥበር፣ ያጎረሰን እጅ መንከስ፣ ያሳደገን ትከሻ መርገጥ፣ ያሳደገው ሀገርም፣ ሕዝብም ተቋምም፣ ማኅበርም የለም፡፡ እንድንኖር ሲባል የሞቱ፤ እንድንድን ሲባል የቆሰሉ፤ እንድንማር ሲባል ያልተማሩ፤ እንድንጠግብ ሲባል የተራቡ፤ እንድንለብስ ሲባል የታረዙ፤ እንድንበለጽግ ሲባል የደኸዩ አሉ፡፡ እነዚህ አካላት ከፍ ያለ ክብር እና ምስጋና ይገባቸዋል፡፡ ስማቸው ከስማችን፤ ክብራቸው ከክብራችን መቅደም አለበት፡፡ ሻካራ እጆቻቸው የስኬታችን መሠረቶች ናቸው፡፡ እናጥባቸዋለን፤ እንስማቸዋለን፣ እንኮራባቸዋለንም፡፡

ያለ እኛ ኖረዋል፡፡ ያለ እነርሱ ግን አንኖርም ነበር፡፡ እነርሱ በእኛ ያበቃሉ፤ እኛ ግን በእነርሱ እንጀምራለን፡፡

ሻካራ እጆች ሆይ ከፍ ከፍ በሉ፤ ክብር እና ምስጋና ለእናንተ ይሁን፡፡ እኛ በእናንተ እንኮራለን፤ እናንተም በእኛ ትጠራላችሁ፡፡ ያለ ሻካራ እጆች ለስላሳ እጆች ከየት ይገኙ ነበር፡፡

ኦ ሸካራ እጆች ሆይ፤ ለሸካራነታችሁ ሰላም እላለሁ እኔን አለስልሶኛልና

ኦ ጠባሳ እጆች ሆይ፤ ለጠባሳችሁ ሰላም እላለሁ፤ እኔን አስውቦኛልና

ኦ የቆሰሉ እጆች ሆይ፤ ለቁስላችሁ ሰላም እላለሁ፤ እኔን አድኖኛልና

ኦ ጎርባጣ እጆች ሆይ፤ ለጎርባጣነታችሁ ሰላም እላለሁ፤ እኔን አክብሮኛልና፡፡

June 11, 2015

                 I KEEP
           MY SELF BUSY
              WITH THE
            THINGS I DO

            BUT EVERY
         TIME I PAUSE,
                I STILL
          THINK OF YOU. 

June 11, 2015

look up to sky and talk to you.
what i wouldn't give to hear you talk back.
I miss your voice,
I miss your laughter,
I miss Everything About you Tata.

Share a story

 
Add a document, picture, song, or video
Add an attachment Add a media attachment to your story
You can illustrate your story with a photo, video, song, or PDF document attachment.