ForeverMissed
Large image
This memorial website was created in memory of our loved one, Engineer Tekletsadik Aberra, 51 years old, born on November 6, 1969, and passed away on February 24, 2021. We will remember him forever.
February 24
February 24
In loving memory of Uncle Tekletsadik, a remarkable civil engineer whose legacy continues to inspire. With a heart full of kindness and a mind brimming with wisdom, he touched countless lives, leaving an indelible mark on all who had the privilege of knowing him.

His dedication to his profession was matched only by his passion for uplifting others, always ready to lend a helping hand and share his knowledge generously. His legacy extends far beyond his professional achievements, for he was a beacon of light, guiding and nurturing those around him to reach their greatest potential.

As we commemorate this anniversary, let us remember Uncle Tekletsadik not with sorrow, but with a profound sense of gratitude for the blessings he brought into our lives. May his example continue to inspire us to be kind, generous, and always willing to lend a hand to those in need. He may have left this world, but his spirit lives on in the hearts of all who knew him.
February 24
February 24
  ተክላይዬ፣ከተለያየን እነሆ ፫ አመታት ተቆጠሩ። ሀዘናችን መሪር ፣እጦታችን ልክ የለሽ ቢሆንም በአጭሩ የሕይወት ዘመንህ የከወንካቸው በጎ ተግባራት የመፅናኛ ምንጮቻችን ሆነዋል። አንተ በብዙዎች ሕይወትና ልብ ውስጥ የዘራሀው የፍቅር፣ የመተሳሰብና የመደጋገፍ ስሜት በጊዜ ርዝመት የማይደበዝዝና በኑሮ ውጣ ውረድ ግዝፈት የማይኮሰምን እንደሆነ በሚገባ አስተውለናል። ለዚህም ነው በዕለት ከዕለት የሕይወት ሩጫችን ወቅት አብረሀን እየተጓዝክ እንደሆነ የሚሰማን።
   ምንጊዜም በልባችንና በሕሊናችን ውስጥ ትኖራለህ። ክበርልን ወንድማችን ።
            ትዕግሥት አበባዬሁና
            ጌታቸው እሸቱ
February 26, 2023
February 26, 2023
To my dear uncle, it’s been two years since your passing, and we continue to think of you everyday. Knowing that you watch over us with the lord makes us strong to continue healing from loosing you. May you continue to rest in peace.
February 26, 2023
February 26, 2023
በእጅጉ የምንወደው ወንድማችን ኢንጂነር ተክለፃዲቅ አበራ ከተለየን እነሆ ዛሬ ሁለት ዓመት ሞላው።አዎ እንዲያው ከተለየን እንበል እንጂ አሁንም በዚህች ዕለት ከእኛው ጋር እየኖረ፣ እንደወትሮው ሰለ እኛ ሲጨነቅና ሲጠበብ ያህል ይሰማናል። አዎ አሁንም እንደቀድሞው የተራቡትን ለማብላት፣ የታረዙትን ለማልበስና አቅመደካሞችን ለመደገፍ ከወዲያ ወዲህ ሲል በዓይነሕሊናችን ይታየናል። ቤተሰባዊ ፍቅሩ፣ትህትናው፣ቁምነገረኛነቱና የበሳል ሀሳብ አፍላቂነት ብቃቱ በብዙዎች ዘንድ ሲነሳና ሲወሳ ይኖራል።
 ልጅ ተክለፃዲቅ፣የደገፍካቸው አቅመደካሞች በፀሎታቸው፣የእውቀት አድማሳቸውን በማስፋት የተሻለ ሕይወት ባለቤት ያደረግካቸው ወጣቶችና በምክርህና በድጋፍህ ያበረታታሃቸው ጓደኞችህ ስለአንተ ማንነት አበክረው በማውሳታቸው ሕያውነትህን አመላክተዋል።


  የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያንም ሐዋርያዊ ተልዕኮዋን ለመወጣት ለምታደርገው ጥረት እውቀትህን፣ገንዘብህንና ጊዜህን በማበርከት ሰለሰጠሀት መንፈሳዊ ግልጋሎት በየእለቱ በስምህ በመጸለይ ኃያሉ አምላካችን ዘለዓለማዊ እረፍትህን በመንግሥተ ሰማያት እንዲያደርግልን እየተማፀነች ነው።


  ውድ ወንድማችን ኢንጂነር ተክለፃዲቅ አበራ በአጭሯ የሕይወት ዘመንህ የፈፀምካቸው በጎ ተግባራት የሕያውነትህ ጉልህ መግለጫ ሆነዋል ።በሠላም እረፍልን ወንድማችን ፣ምንጊዜም በልባችንና በሕሊናችን ውስጥ ትኖራለህ ።
                   ትዕግሥት አበባዬሁና
                   ጌታቸው እሸቱ
February 25, 2023
February 25, 2023
Oh My dear brother two years gone with ....
Love you lots. God may rest your soul in heaven 



February 25, 2023
February 25, 2023
Two years has gone since we lost you. I miss you terribly but will never forget your memory !!!!
February 25, 2022
February 25, 2022
A year has passed and the pain from loosing you still hurts but living through your memories I know that we must look forward and continue to better ourselves the way you would help us. Through this last year there has been many changes but keeping you in the forefront of my mind has helped us get to and achieve goals you would be proud of. Long live and god bless you my great uncle Teklai.
February 24, 2022
February 24, 2022
እንዴትከረምክ ወንድሜ መቸም ያንተን ነገር ሲያስቡት ሁልጊዜ እውነት እውነት እይመስልም ግን ዛሬ እንደኛ እመትህ እዪተከበረ ነው ያንተ ነገር ከባድ ቢሆንም  ምንም ማድረግ እይቻልም ወንድሜ ሁል ጊዜ ስትታስብ ትኖራለህ በአፀደ ገነት ያኑርህ

        ትግስት አበባዪሁ
February 22, 2022
February 22, 2022
ተክላይዬ አንድ አመት ሊሆንህ ሁለት ቀን ይቀረዋል ጌታቸውም እዲስ እበባ ሄዷል ወንድሜ እኔም ከፍኝ አለመሄዴ ሁል ጊዜ እንተን በማስበት ጊዜ አእምሮየም ሆዴም ይታመማል አንተ አንድ ስው ብቻ እልነበርክም በተለይ በስው አገር ላይ ሆኖ ያንተ ነገር ያማል እገራችን እንገባለን ወንድማችን አለ ብለን ከነልጆቻቾን ተመክተንብህ ነበር ብቻ እምላክ ሁሉም ነገር በሱ ፈቃድ ነው የሚሆነው የሆነው ሆነ ተክላይዬ ሁልጊዜ በሀሳባችን ትኖራለህ እምላክ በገነት ያኑርህ
       ከትእግስት አበባዪሁ
February 7, 2022
February 7, 2022
ወንድሜ  ከዚህ አለም ውጣውረድ ማረፍክን በዓመትህ ስስማ ውስጤ ታመመ፡፡በጣምም አዝኛለሁ፡፡ከዩኒቨርስቲ ጅምሮ እስከአሁን ሰዓት ድረስ ያለን ቅርርበት ጥሩ ነበር፡፡ባለውለታዬ አማካሪዬ ነበርክ፡፡አሁን ባዶነት ተሰማኝ፡፡ቢያንስ አፈር ባለብስህ ጥሩ ነ በ ር፡፡ግን አልተፈቀደም፡፡የምታከብራቸው ስላሴዎች ነፍስህን በአፀደ ገ ነ ት ያኑሩት፡፡እያለቀስኩኝ ለውድ ወንድሜ የጻፍኩት ማስታወሻ ነው፡፡
አትናስዮስ እና ይርጋ በርቱ የተጀመሩትን ፕሮጀክቶች ለመጨረስ ሞክሩ፡፡የወንድማችን ስም በጥሩ ማስጠራት ይኖርብናል፡፡የሙያ እገዛ ካስፈለገ ዝግጁ ነኝ፡፡
ኢንጅነር ከ በ ደ በቀለ 0911612662
November 7, 2021
November 7, 2021
 No gift could ever match the gift of love and affection you have given us all these years. We may not be able to spend time with each other, but you will always be in our heart and mind. I wish on this special day may your Light shine beyond the veil.

        HAPPY BIRTHDAY!!
          
                 Mikiyas Getachew
                 Eshetu Haile Tefera
November 6, 2021
November 6, 2021
Happy Birthday to the late great Teklai. As time goes on the memory of you will never fade. May you continue to Rest In Peace.
November 6, 2021
November 6, 2021
 
መልካም ልደት ውድ ወንድማችን ተክለጻዲቅ አበራ
ተክልዬ የቤተሰባችን ፍቅርና ትስስር ጥንካሬ መሠረትነትህ የእምነት ጽናት ተምሳሌትነትህ የበጐ ምግባርና የአገር ፍቅር ስሜት መግለጫ የነበሩት ተግባራትህ ለእኛ ብቻ ሳይሆን ለልጅ ልጆቻችን ጭምር የሚተላለፉ የሕያውነትህ መግለጫዎች ናቸው
  ውዱ ወንድማችን በአጭር የሕይወት ዘመንህ የተቸገሩን በመርዳት ደካሞችን በመደገፍ የእውቀት ጥማት የነበራቸውን ወጣቶች በማስተማር ለቁም ነገር ያበቃቸው ሁሉ በሕልፈትህ በእጅጉ ያዘኑ ቢሆኑም ድጋፍህና እርዳታህ ምክርህና ማበረታታትህ በሕይወታቸው ላይ ያስከተለውን በጐ ተፅዕኖ በመመልከት ሕያውነትህን በገሀድ እያስመሰከሩ ነው
  ምንጊዜም ቢሆን በሕሊናችንና በልቦናችን ውስጥ ትኖራለህ!! እንኳን ተወለድክልን!!
                 ትዕግስት አበባዬሁ
                 ጌታቸው እሸቱ
  
 
May 27, 2021
May 27, 2021
 ወንድሜ አባቴ አባ ከፋኝ እምባዬ አላፅፍሽ አለኝ የአዘንሽበትን ነገር ስትፅፊው ይቀልሻል ፃፊው ትለኝ ነበር ግን-------አንድ ቀን እፅፋለሁ ይቀመጥ በሆዴ እንዳይቀለኝ አቡዬ ወዳጅህ ይቀበሉልኝ!!

ናፋቂህ እህት ቅድስት አበራ
May 22, 2021
May 22, 2021
In my heart you will always hold a special place.
All the good times we’ve shared,
the memories we’ve made.
Every day I think about them all,
From my mind they will never fade.
How I wish we could walk arm in arm, hand in hand, heart to heart.
If I would’ve known that it would end like this,
I thought we’d never have to be apart.

So many questions I still have to ask,
my best friend gone.
Why?
You were too young to go,
it didn’t have to be like this, you didn’t have to die.
From now until the end of my life you will be on my mind,
every minute,
every hour,
every day.
I miss you,
and this is how it will stay
May 21, 2021
May 21, 2021
ነፍስህ በደጋጎቹ እቅፍ ያኑርልኝ

Shared by Yirgalem Abera Sahel on May 17, 2021

ተወዳጁ ወንድሜ የእኛን አስተዳደግ መቼም በዙሪያችን ያለ ሁሉ ያውቀዋል ከልጅነት ጀምሮ ለአንተ ያለን ክብር እና ፍቅር የማይለዋወጥ ነበር።አንተ ማለት ለእኛ ወንድምም አባትም ጓደኛም ነበርክ። አንተ ማለት ለዚህ ቤተሰብ ምሰሶ ነበርክ ከልጅነት ጀምሮ ኮትኩተህ አሳድገህ ፣አስተምርህ ፣ድረህ ለቁምነገር አብቅተህናል የተለየህ ሰው ነበርክ ሁሌም ቢሆን ከልቤ አትጠፋም በምንም ቋንቋ ስለአንተ መግለፅ አይቻልም አንተ የብዙ ሰው ተስፋ ነበርክ ከአንተ እግዚአብሔን መፍራት፣የቤተሰብ ፍቅርን ፣የዘመድ ፍቅርን፣ለሙያ መታመንን፣ለሰው መኖርን ተምሬአለሁ አንተ የሕይወት መምህሬ ነበርክ አንተ የቤተሰቦችህን ብቻ ሳይሆን በዘሪያህ ያሉ ሰዎችን ሁሉ ሕይወት ቀይረሀል በዚህም ሁሌም እኮራብአለሁ ውዱ ወንድሜ አንድ ሰው በሕይወት ዘመኑ መስራት የሚገባውን በጎ ስራ ሁሉ ሰርተሀል ሁሌም እንደምትለው "ሰው ለራሱ ብቻ ከኖረ ምን ዋጋ አለው" እናም ያንተን ፈለግ ለመከተል ቃል እገባለሁ እንግዲህ ወንድሜ በህልም እየመሰለኝ እኖራለሁ እግዚአብሔር ነፍስህን በገነት ያኑርልኝ በየደቂቃው አስብህአለሁ!!             

      አክባሪ ወንድምህ  ይርጋለም አበራ
                 ግንቦት 09/2013
May 20, 2021
May 20, 2021
 In honors and memory of my beloved uncle and father Tekletsadik Aberra. Even though I was not fortunate enough to have spent time with you, but I am grateful to have had all the conversations over the phone throughout the years and especially on the holidays which I cherished greatly. I may not have the chance to personally show you the fruits of all your advices and mentorship but certainly they have not gone unheard. I want to say from the bottom of my heart thank you for having a loving and caring nature for someone on the other side of the world and for always embracing with an open arms. I will forever remember you not in the tears shed, nor in the sadness felt,but with a smile, happiness, gratitude for all the blissful love you have instilled within myself and my family. May you live on in all of us.
 A shining example, my uncle and father of the best of the Children of Light.

"Judge not a child of the light by the mount of their gold nor by the size of their intellect but by the size of their heart."

May 19, 2021
May 19, 2021
የምወድህ አክባሪዬ ወንድሜ መቼም የማልረሳህ የደጎች ምሳሌ የሆንክ ይህ ክፉ ጌዜ በግድ አለያየን ሁሌም እናስብሀለን እግዚአብሔር በአብርሀምና በይስሀቅ ጎን ነፍስህን ያርግልን።

አክባሪ እህትህ እርስቴ
May 18, 2021
May 18, 2021
ውድ ወንድሜ የማከብርህ የምወድህ ከሩቅ የምታይብህ ሰንደቄ ፣ የምጠለልብህ ጥላዬ ፣ ክፉውን የምመክትብህ ጋሻዬ ፣ የምኮራብህ መኩሪያዬ ነበርክኮ አሁን ይህ ሁሉ ቀርቶብኝ አለቅሳለሁ
ለካ ታላቅ ወንድም አለኝ ማለት ኩራት ነበር ፣ አሁን ነው የገባኝ ምንቸገረኝ እርሱ አለ የምለው ለካ ቀላል አልነበረም አሁን ተረዳሁ።
ወንድሜ የፊደል ብቻ ሳይሆን የመንፈሳዊ ህይወት መምህሬም ነበርክ፣ የመጀመሪያ ጸሎትን ያስተማርከኝ ለዛሬ ማንነቴ መሰረት
አንተ ነህ ።
እንደ አባት አሳድገህ፣ እንደ ወንድም መክረህ፣ እንደ ጓደኛ አማክረህ ለዚህ አበቃኸኝ ሁሌም አመሠግንሀለው። እግዚአብሔርን መፍራት፣ ለእናት አባት መታዘዝ፣ ታላላቅን ማክበር፣ ለሰዎች መታመን፣ ሥራን መውደድ፣ ቃልን መጠበቅ፣ ከሁሉ ተዋዶ ተከባብሮ መኖርን ካንተ ተምሬአለሁ በዚህም ሁሌም አመሠግንሀለዉ።
ወንድሜ ትንሽ ብትቆይልን ምን ነበር?!
ምን ማድረግ ይቻላል ሁሉ በእግዚአብሔር ፈቃድ ነውና
ብዙ ባልኩ ደስ ባለኝ ግን አልቻልኩም
ውድ ወንድሜ ሁሌም በልቤ አለህ በብዙ መልካም ሥራዎችህ ከኔ ጋር አለህ
እግዚአብሔር በመልካሙ ቦታ እንደሚያሳርፍህ አምናለሁ አልጠራጠርምም
እረፍልኝ
ሁሌም በማንኛውም ጊዜና ሠዐት አስብሃለው

ናፋቂህ ወንድምህ አትናቴዎስ አበበራ

May 16, 2021
May 16, 2021
To my great uncle Teklai
Life has shown me the importance of family and hard work, but you showed me the most important thing in life, and that is having faith in my family and myself. Growing up in America we never got to see each other much. In 2019 I visited for the first time. You took us in and treated us like we were one of your own. In my short time out there you taught me the value of family and instilled in me to have faith in myself. You showed me the most important thing in life is having faith in God and my family. I will stride everyday to live to those values and accomplish all the things you knew I would. For that I thank you. ,
May 16, 2021
May 16, 2021
የኢንጅነር ተክለጻዲቅ አበራ ሕልፈት ፍፁም ያልጠበቅነው ዱብ ዕዳ በመሆኑ በመላው ቤተሰባችን ዘንድ የፈጠረው ድንጋጤና ጥልቅ ሀዘን ከፍተኛ ነው። ተክለጻዲቅ የቤተሰባችንን ፍቅር ፣ ግንኙነትና ትብብር በማጠናከር በኩል ያበረከተው ድርሻ እጅግ የጎላ ነበር። በዚህም የተነሳ በሕልፈቱ ከቤተሰባችን ጠንካራ ምሰሶዎች አንዱና ዋንኛውን ተነጥቀናል።
ብዙዎች ተክለጻዲቅ አበራን የተራቡን በማብላት፣ የታረዙትን በማልበስ፣ የተቸገሩን በመርዳት ውጤታማ ጥረቱ በሚገባ ያውቁታል ።ውድ ወንድማችን ዕውቀቱን፣ገንዘቡን ጊዜውን በመቸር የብዙዎችን ተስፋ እውን ለማድረግ ከመጣሩ ባሻገር የመንፈሳዊ ሕይወቱ ጥልቅ መሠረት የሆነችውን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ለማጠናከርም በተቻለው ሁሉ ምሳሌነት ያለው ተግባር ፈጽሟል።
ልጅ ተክለጻዲቅ አቅዶ የመፈፀም፣ጀምሮ የመጨረስና ተናግሮ የማሳመን ችሎታና ብቃቱም ከፍተኛ ነበር።በዚህ በኩል በተለይ በውጭ ሀገር ያሳደግናቸው ልጆቻችንን ስለኢትዮጵያና ኢትዮጵያዊነት ያላቸው ግንዛቤና ፍቅር ከፍ እንዲል በማድረግ በኩል ያበረከተልን ድጋፍ እጅግ ከፍተኛ ነበር። ቅዳሜ ቅዳሜ ከቤተሰባችን ጋር የሚደርገውን የስልክ ጭውውት ልጆቻችን በልዩ ጉጉት ነበር የሚጠባበቁት። አሁን ያሁሉ በመቅረቱ በሁላችንም ዘንድ ትካዜና ሀዘን ሰፍኖብናል።
የውድ ወንድማችን ሕልፈት ያሳድርብን ሀዘን መራር ቢሆንም፣ አጭር የሕይወት ዘመኑን የሰዋባቸውን ጅምር ተግባራት አጠናክሮ በመቀጠል ስሙና ምናቡ ለተከታታይ ትውልዶች በክብር እንዲተላለፍ የማድረጉ ኀላፊነት በእኛ ላይ የወደቀ መሆኑን ተገንዝበናል ።ለዚህም ክብር እንድንበቃ እግዚአብሔር ብርታቱን ይሰጠን ዘንድ እንጸልያለን ።
                 ትዕግስት አበባዬሁና
                 ጌታቸው እሸቱ

Leave a Tribute

Light a Candle
Lay a Flower
Leave a Note
 
Recent Tributes
February 24
February 24
In loving memory of Uncle Tekletsadik, a remarkable civil engineer whose legacy continues to inspire. With a heart full of kindness and a mind brimming with wisdom, he touched countless lives, leaving an indelible mark on all who had the privilege of knowing him.

His dedication to his profession was matched only by his passion for uplifting others, always ready to lend a helping hand and share his knowledge generously. His legacy extends far beyond his professional achievements, for he was a beacon of light, guiding and nurturing those around him to reach their greatest potential.

As we commemorate this anniversary, let us remember Uncle Tekletsadik not with sorrow, but with a profound sense of gratitude for the blessings he brought into our lives. May his example continue to inspire us to be kind, generous, and always willing to lend a hand to those in need. He may have left this world, but his spirit lives on in the hearts of all who knew him.
February 24
February 24
  ተክላይዬ፣ከተለያየን እነሆ ፫ አመታት ተቆጠሩ። ሀዘናችን መሪር ፣እጦታችን ልክ የለሽ ቢሆንም በአጭሩ የሕይወት ዘመንህ የከወንካቸው በጎ ተግባራት የመፅናኛ ምንጮቻችን ሆነዋል። አንተ በብዙዎች ሕይወትና ልብ ውስጥ የዘራሀው የፍቅር፣ የመተሳሰብና የመደጋገፍ ስሜት በጊዜ ርዝመት የማይደበዝዝና በኑሮ ውጣ ውረድ ግዝፈት የማይኮሰምን እንደሆነ በሚገባ አስተውለናል። ለዚህም ነው በዕለት ከዕለት የሕይወት ሩጫችን ወቅት አብረሀን እየተጓዝክ እንደሆነ የሚሰማን።
   ምንጊዜም በልባችንና በሕሊናችን ውስጥ ትኖራለህ። ክበርልን ወንድማችን ።
            ትዕግሥት አበባዬሁና
            ጌታቸው እሸቱ
February 26, 2023
February 26, 2023
To my dear uncle, it’s been two years since your passing, and we continue to think of you everyday. Knowing that you watch over us with the lord makes us strong to continue healing from loosing you. May you continue to rest in peace.
His Life
May 15, 2021
የኢንጂነር ተክለጻዲቅ አበራ አጭር የሕይወት ታሪክ

ኢንጂነር ተክለጻዲቅ አበራ ከአባታቸው ከአቶ አበራ ሳህሌ እና ከእናታቸው ከወ/ሮ አልማዝ አሳመረ ጥቅምት 27 ቀን 1962 ዓ.ም በአዲስ አበባ ልዩ ስሙ አማኑኤል በሚባለው አካባቢ ተወለዱ፡፡ እድሜአቸው ለትምህርት ሲደርስ በቄስ ት/ቤት ገብተው ከፊደል አስከ ዳዊት ንባብ ድረስ ከዘለቁ በኋላ በየካቲት 23 1ኛና መለስተኛ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት ከ 1ኛ እስከ 8ኛ ክፍል ተምረዋል፡፡ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርታቸውን በኮልፌ አጠቃላይ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት ተምረው በከፍተኛ ውጤት በማጠናቀቅ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ቴክኖሎጂ ፋኩሊቲ በመግባት በሲቪል ምህንድስና ተመርቀዋል፡፡ የዩኒቨርሲቲ ትምህርታቸውን በጥሩ ውጤት ካጠናቀቅ በኋላ ወደ ሥራ ዓለም በመግባት በአድማስ ኮንስትራክሽንና በሳትኮን ኮንስትራክሽን ድርጅቶች ከሳይት መሀንዲስነት እስከ ፕሮጀክት ሥራ አስኪያጅነት አገልግለዋል፡፡ በተለይም በሳትኮን ኮንስትራክሽን ቆይታቸው

1ኛ. የሰቆጣ ሆሰፒታል ግንባታ በፕሮጀክት ሥራ አስኪያጅነት

2ኛ. በጅጅጋ የመምህራን ማሰልጠኛ ግንባታ በፕሮጀክት ሥራ አስኪያጅነት

3ኛ. በመቀሌ፤አድዋ፤ አክሱምና ሽሬ የከፍተኛ ኃይል ማስተላለፊያ ጣቢያ // ሰብ ሰቴሽን/ ግንባታ የሁሉም ፕሮጀክቶች ሥራ አስኪያጅ በመሆን ሰርተዋል፡፡

እነዚህን ፕሮጀክቶች ሲመሩ እድሜአቸው ከ 30 ዓመት በታች የነበረ ሲሆን ባላቸው የሥራ ቁርጠኝነት፤ አመራርና አፈጻጸም ከሥራ ባልደረቦቻቸውና ከበላይ አለቆቻቸው ልዩ ክብርና አድናቆት ይሰጣቸው የነበሩ ትጉህ ሠራተኛ ነበሩ፡፡

1991 ዓ.ም ጀምሮ የግላቸውን ታብኮ ኮንስትራክሽን የተባለ ድርጅት በመክፈት ሥራ የጀመሩ ሲሆን በዚህም ቆይታቸው እስከ ሕይወት ህልፈት ድረስ በሚወዱት ሙያቸው ቤተሰቦቻቸውን፤ ወገኖቻቸውን፤ ህዝባቸውንና አገራአቸውን በቅንነት አገልግለዋል፡፡ በግል መስራት ከጀመሩ ወዲህ ከ300 በላይ የመኖሪያ ቤቶች፤ ከ20 በላይ የንግድ ህንጻዎች፤ በሚዛን ቴፒ እና ወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ ፕሮጀክቶች፤ በቤቶች ልማት የ20/80 እና 40/60 ፕሮጀክቶች፤ በህዝባዊና ልማት ድርጅት ፕሮጀክቶች ላይ በብዙ የተሳተፉ፤ ለብዙ ወገኖች የሥራ እድል የፈጠሩ፤ የሥራ ሥነ-ምግባርና መርሆዎችን አክብረው የሚሰሩ ታላቅ አገር ወዳድ ሰው ነበሩ፡፡

ኢንጂነር ተክልጻዲቅ አበራ በዚሁ ሁሉ የሥራ ኃላፊነት ውስጥ እያሉ እንኳን  ለመማር ካለቸው ጽኑ ፍላጎት ትምህርታቸውን በመቀጠል ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በሀይድሮሎጂ ኢንጂነሪንግ የማስተርስ ዲግሪያቸውን አግኝተዋል፡፡

ኢንጂነር ተክለጻዲቅ አበራ በማኅበራዊ ሕይወታቸውም እጅግ መልካም የነበሩ ሲሆን በአካባቢ ልማት፤ በወላጅ አልባ ህጻናትና አረጋውያን እንክብካቤ፤ በአብያተ ከልርስቲያናት ግንባታ እጅግ የላቀ ተሳትፎ ያደርጉ ነበር፡፡

ይህንን ሁሉ ሲያደርጉ ለሰዎች መታየትን ካለመፈለጋቸው የተነሳ ያደረጉትን አስተዋጽኦ ሁሉንም መግለጽ ባይቻልም በቁጥር በውል የማይታወቅ ወላጅ አልባ ልጆችና አራጋውያንን ይረዱ ነበር፡፡

ከአብያተ ክርስቲያናት ግንባታ ከብዙ በጥቂቱ

1ኛ. በሰሜን ሸዋ ዞን በእንሳሮ ወረዳ የምትገኘው የሐመረ ኖኅ ጠገራ ቅድስት ማርያም ቤ/ክ በእውቀታቸው፤ በሙያቸውና በገንዘባቸው ከፍተኛ አስተዋጽኦ በማድረግ የሰሩ ሲሆን አሁንም ከዚህ ቀደም ተሰርቶ የነበረው ቤ/ክ በመጥበቡና በማርጀቱ እንደገና በመሰራት ላይ ላለው ቤ/ክ ከዲዛይን ጀምሮ በሙያና በገንዘብ ከፍተኛ አስተዋጽኦ በማድረግ እየሰሩ የነበሩ ሲሆን ለአገልጋዮችም በዘላቂነት ወርሃዊ ደሞዝ በመክፈል ያስገልግሉ ነበር፡፡

2ኛ. በሰሜን ሸዋ ዞን በመርሐቤቴ ወረዳ የመሳኖ አይኔ ሜዳ ቅዱስ ሚካኤል ቤ/ክ በሙያቸውና በገንዘባቸው ሰርተዋል በዘላቂነትም አገልጋዮች የሚያስፈልጋቸውን በማሟላት እንዲገለገል አድረገዋል፡፡   

3ኛ. በአዲስ አበባ አገረ ስብከት የቀበና መድሐኔዓለም ቤ/ክ ከጅምሩ እስከ ፍጻሜው ድረስ ደከመኝ ሰለቸኝ ሳይሉ በዋና አማካሪነት አገልግለዋል በግንዘባቸውም ከፍተኛ አስተዋጽኦ አድርገዋል፡፡

4ኛ. በአዲስ አበባ አገረ ስብከት የአያት ጌቴ ሴማኒ ቅድስት ኪዳነ-ምህረትና ቅዱስ ገብርኤል ቤ/ክ የቴክኒክ ኮሚቴ በመሆን ግንባታው አሁን ያለበት ደረጃ እንዲደርስ በገንዘባቸውም በሙያቸውም ከፍተኛ አስተዋጽኦ አበርክተዋል፡፡

ኢንጂነር ተክለጻዲቅ አበራ በዚህ ጽሁፍ ያልተካተቱ በርካታ ሥራዎችን የሰሩ ታላቅ ሰው ነበሩ፡፡

ኢንጂነር ተክለጻዲቅ አበራ በትዳር ሕይወታቸውም ከወ/ሮ አልማዝ እሸቱ ጋር ላለፉት 22 ዓመታት በፍቅርና በመከባበር ለሌሎች አርአያ የሚሆን የትዳር ዘመንን አሳልፈዋል፡፡ በዚህ ዘመናቸውም ከባለቤታቸው ጋር በመሆን ታናናሽ ወንድምና እህቶቻቸውን እንደ አባት አስተምረው እንደ ወንድም መክረው ከፍ ላለ ቁምነገርና ሕይወት አብቅተዋል፡፡ ከዚህም በተጨማሪ አምስት ሴትና አንድ ወንድ ልጅ ኣሳድገው አስተምረው ለከፍተኛ ተምህርትም አብቅተዋል፡፡

ኢንጂነር ተክለጻዲቅ አበራ እግዚአብሔርን የሚፈሩ፤ ሰውን የሚያከብሩ፤ መልካን የሚሰሩ፤ ብዙ ከመናገር ብዙ መስማትና መስራት የሚያዘወትሩ መልካም የእግዚአብሔር ልጅ ነበሩ፡፡

በዚህ ዓለምም ስትኖሩ ተዘጋጅታችሁ ጠብቁ ያለውን አምላካዊ ቃል ፈጽመው በሥጋውና ደሙ ታትመው የከበሩ በመሆናቸው እረፍት እንጂ ሞት የለባቸውምና ወደ ዘላለም ቤታቸው ወደ ቸሩ አባታቸው ወደ እግዚአብሔር ሄደዋል፡፡

ኢንጂነር ተክለጻዲቅ አበራ ምንም እንኳን ከዚህ በላይ ቢቆዩና ከዚህም በላይ ብዙ መልካም ሥራ እንዲሰሩ ብንመኝም አምላክ ፈቃዱ የሆነው የቆይታቸው ጊዜ ይህ ነውና ባደረባቸው ህመም በህክምና ሲረዱ ቆይተው በተወለዱ በ51 ዓመታቸው የካቲት 17 ቀን 2013 ዓ.ም ከዚህ ዓለመ-ድካም አርፈው የካቲት 18 ቀን 2013 ዓ.ም በደ/ም/ቅ/ሰአሊተ ምሕረትና ቅድስት ክርስቶስ ሰምራ ካቴድራል ቤተሰቦቻቸው፤ ያገለገሉባት ቤ/ክ አገልጋይ አባቶች ካህናትና ወዳጅ ዘመዶቻቸው በተገኙበት በታላቅ ክብር ሥርዐተ-ረፍታቸው ተፈጽሟል፡፡                            



ነፍሴ ሆይ ወደ ዕረፍትሽ ተመለሺ፤ እግዚአብሔር መልካም አድረጎልሻልና፤ ነፍሴን ከሞት ዓይኔንም ከእንባ እግሬንም ከመሰናክል አድኖአልና በሕያዋን አገር በእግዚአብሔር ፊት እሄዳለሁ መዝ. 115 ፡ 7-9

Recent stories
February 26
ውድ ውንድሜ እንዴት ነህ አንተን እስክሆን መቼም አልረሳህ ሁሌም እወድሃለው 
ሦስት ዓመት…እህ
February 26, 2023
ውዱ ወንድሜ እንደቀልድ ከተለየህን ይህው ሁለት ዓመት ሆነው አንድም ቀን ሳላስታውስህ ውዬ አላውቅም   ሁሌም በልቤ ትኖራለህ እግዚአብሔር ነፍስህን በገነት ያቆይልኝ
አክባሪ ወንድምህ ይርጋለም አበራ።
የካቲት 19/2015
November 6, 2022
ውድ ወንድሜ ዛሬ ፶፫ኛ (53ኛ) የልደት በዓልህን እያከበርን ነው ከኛ ጋር በአካል ባትኖርም ሁልጊዜም በመንፈስ ከኛ ጋር ነህ እግዚአብሔር ነፍስህን ከደጋጎች ጋር ያሳርፍልኝ
ወንድሜ ሁሌም እወድሃለው
አትናቴዎስ አበራ

ጥቅምት ፳፯ ቀን ፪፼፲፭ ዓም
ጥቅምት 27 ቀን 2015 ዓም

Invite others to Engineer Tekletsadik's website:

Invite by email

Post to your timeline